The Assosa Tigreans killing was planned in advance and local authorities knew about it
May 16, 2014The killings of 9 Tigreans in Assosa were planned in advance and the local authorities knew about it, according to Abraha Desta, an ARENA party member from Mekele.
ባለፈው ሳምንት 9 የትግራይ ተወላጆች በቤኑሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ ታርደው መገደላቸው ይታወሳል። አንድ ሌላ የታክሲ ሹፌርን በጥይት ተገድሏል (ከትግራይ)። በአንድ የዕጣን ድርጅት ይሰሩ የነበሩ ሦስት የአማራና ኦሮምያ ክልል ተወላጆችን ተገድለዋል። ትናንት ሐሙስ ግንቦት 7ም አንድ መኪና በታጣቂዎች ተይዞ በእሳት ጋይቷል። በተሳፋሪዎቹ የደረሰ ጉዳት በትክክል ባይታወቅም አንዲት ተሳፋሪ ግን ቆስላ ተገኝታለች።
በ9ኙ የትግራይ ተወላጆች ላይ የደረሰውን ግድያ ለማጣራት በመኮርኩት መሰረት ግድያው ሆን ተብሎ ታቅዶ የፈፀመ ስለ መሆኑ አረጋግጫለሁ። ሙሉ መረጃ ያላቸው አሶሳ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች እንዳረጋገጥሉኝ ከሆነ ዓማፂ ቡድኑ የትግራይ ሰዎችን አርዶ ለመግደል ማቀዱ ይታወቅ ነበር። የወረዳው አስተዳዳሪ ይህን መረጃ ከግድያው በፊት ደርሶታል። ባከባቢው የሚገኘው የመከላከልያ ሰራዊት አዛዥም ግድያ እንደሚፈፀም ተነግሮታል። ባጠቃላይ መንግስት ግድያው በተመለከተ ሙሉ ቅድመ መረጃ ነበረው። መንግስት መረጃ እያለው ግድያው መከላከል አለመቻሉ ኗሪዎችን አሳዝኗል። በአሶሳ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች መንግስት ተገቢውን ፀጥታ የማስከበር ተግባር አለመፈፀሙ አስገርሟቸዋል። መንግስት ለስልጣኑ እንጂ ለህዝብ ደህንነት እንደማይተጋም አስረግጠዋል። አሁንም አሶሳ አከባቢ የሚኖሩ የሌላ ክልል ተወላጆች ስጋት ዉስጥ ናቸው።
መንግስት በትግራይ ልጆች ላይ ግድያ እንደሚፈፀም እያወቀ ለምን መከላከል እንዳልቻለ ለህዝብ መግለፅ ይኖርበታል። የሰለማዊ ሰዎች ደህንነት መጠበቅ ባለመቻሉም ይቅርታ ይጠይቅ፣ ተገቢውም ካሳ ይክፈል።
ዘጠኝ የትግራይ ተወላጆች በአሶሳ ታርደው መገደላቸውን አብርሃ ደስታ ከመቀሌ ዘገበ!
ከአብርሃ ደስታ ፌስቡክ የተወሰደ፡“ባለፈው ሳምንት የጉልበት ሥራ ለመስራት በአንድ ኮንትራክተር ተቀጥረው ወደ አባይ ግድብ በደህንነት መኪና ሲጓዙ ከነበሩ 28 የትግራይ ተወላጆች ዉስጥ ዘጠኙ ታርደው ሲገደሉ የተወሰኑም ቆስለዋል። ባለፈው ቅዳሜ ደግሞ አንድ የትግራይ ተወላጅ በተመሳሳይ ተገድሎ ተገኝቷል። ቀጥሎም በአንድ ድርጅት ሲሰሩ የነበሩ ሦስት ሰራተኞች መገደላቸው ተሰምቷል። ገዳዮቹ ከኢህአዴግ ጋር የተጣላ የአንድ ዓማፂ ቡድን አባላት ናቸው።የሕወሃት አገዛዝ እንደሚፈልገው፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ የዱር አውሬ ይመስል እርስ በርሱ ከመባላት ተቆጥቦና አንደነቱን አጠናክሮ፡ ዘረኛውን አገዛዝ ከሥልጣን አውርዶ ለፍርድ ማቅረብ ብቻ ነው የሚጠበቅበት።
ባከባቢው የፌደራል ፖሊሶችና መከላከያ ሰራዊት አባላት ቢገኙም ወንጀሉ መከላከል እንዳልቻሉ ታውቋል። ሁኔታው ለማረጋጋት ሲሉ አቶ ፀጋይ በርሀና አቶ አዲሱ ለገሰ ወዳከባቢው ቢጓዙም የተለመደ ፖለቲካ ከመስበክ የዘለለ ነገር አላደረጉም። መንግስት ፀጥታን ማስከበር ይገባዋል። ደግሞ ሰለማዊ የቀን ሰራተኞች በደህንነት መኪና መጫን ተገቢ አይደለም። በደረሰ ጉዳት ጥልቅ ሐዘን ይሰማናል።
ወላዲት ትግራይ መዓዝ ይኾን ሓዘንኪ ዘብቅዕ?”
የትግራይ ሕዝብም፡ አንደነቱን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር አጠናክሮ፡ ደህነንቱን ሳይሆን ጥፋትን ወደ እርሱ አቅጣጭ እየገፉበትን ያሉትን በስሙ የሚነግዱትን ጠላቶቹን ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር በጋራ መፋለም ይኖርበታል!
በመካከላችን ያለችው አንድ በጋራ የምንካፈላት ኢትዮጵያ – የሁላችንም አገር – ስለሆነች የጥቂት ዘረኞች ብቻ እንዳትሆን ባለን ኃይል ሁሉ ልንፋለም ይገባናል!
No comments:
Post a Comment